የዛሬ YeZare.com
Welcome
Login / Register

What is the proper amount of sleep Time

ምንያህል የእንቅልፍ ሰዓት በቀን ያስፈልገናል?

 

(በዳንኤል አማረ )

 

የድካም ስሜት ቀን ላይ ይሰማዎታል? በቂ የሆነ እንቅልፍ ማግኝትዎን እርግጠኛ ነዎት? እንቅልፍ ደስታን የሚሰት አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ በህይወታችን ለሚያጋጥሙን ችግሮች መልስ ብቻ ሳይሆን ጤናማ እንድንሆን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለአእምሮ ጤንነት እና መደበኛ ተግናሩን በትክክል ያለምንም ችግር እንዲወጣ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የተላያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቂ እንቅፍ ማግኝት ነገሮችን ለማስታወስ፣ መረጃዎችን ለማሰላሰል እና አዲስ ነገሮችን ለመማር አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

 

ስለዚህ በቂ የሆነ እንቅልፍ ያገኛሉ?
የአሜሪካ ብሄራዊ እንቅልፍ ማህበር በቀን ምን ያህል የእንቅልፍ ሰዓት እንደሚያስፈልገን እንደሚከተለው አስቀምጧቸዋል፦

፨ህፃናት(Infants)፦ ዕድሜያቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ
በቀን እስከ 16 ሠዓት ያስፈልጋቸዋል፡፡(የቀን እረፍትን(ናፕ) ጨምሮ)

፨ከፍ ያሉ ህፃናት(Toddlers)፦ ዕድሜያቸው ከ 1-3 ዓመት የሆነ በቀን ከ 12-14 ሠዓት እንቅልፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡(የቀን እንቅልፍን ወይም ናፕን ጨምሮ)

፨ለቅድመ ትምህርት የደረሱ፦ ዕድሜያቸው ከ 3-5 ዓመት የሆነ በቀን ከ 11-13 ሠዓት እንቅልፍ ያስፈልጋቸዋል

፨ለትምህርት የደረሱ፦ ዕድሜያቸው ከ 6-12 ዓመት የሆነ
በቀን ከ 10-11 ሠዓት እንቅልፍ ያስፈልጋቸዋል

፨ታዳጊ/ወጣት(Teens)፦ ዕድሜያቸው ከ 13-19 ዓመት የሆነ በቀን ከ8.5-9.5 ሠዓት ያስፈልጋቸዋል፡፡

፨ አዋቂዎች(Adults)
በቀን ከ 7-9 ሠዓት ያስፈልጋቸዋል፡፡

መልካም እንቅልፍ!!

 

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles

RSS